Study on-line

Study on-line (310)

A to Z is a collection of resources for Ethiopian's legal profession, students, academics and the public. These links have been collected so that users with an interest in the law and Ethiopia may be able to access the Ethiopian legal information they require more quickly. The site is organized simply into an alphabetical list of law subjects. This link is a very helpful source for students who want to study online as teaching materials written by different university teachers under the sponsorship of Justice and Legal System Research Institute are included in the list. Moreover, Training materials prepared by different Proffessionals under the sponsorship of Federal Justice Organs Professionals Training Centerare also in our list. 

ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቃሳቀስ በሚል የተደረገ የንብረት ክፍፍል ይህ ክፍፍል መሰረት የሚያደርገው ግዙፋዊ/ቁሳዊ ህልውና ያላቸውንና በስሜት ህዋሶቻችን ሊታወቁ የሚችሉትን ነገሮች ናቸው።   ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፦   ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የምንላቸው በራሳቸው ወይም በሰው ጉልበት ጉዳት ሳይደርስባቸው ወይም ተፈጥሮኣዊ ባህሪያቸውን ሳይቀይሩ ሊጓዙ ወይም ሊጓጓዙ የሚችሉ ግዙፋዊ ህልውና ያላቸው ናቸው። ስለዚ አንድ ንብረት ተንቀሳቃሽ ነው…
በሕግ እውቅና የሚያገኙና ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች የገንዘብ ዋጋ(Pecuniary Value) ያላቸው ሆኖው ከአንድ ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉና በገንዘብ ዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ ተብለው በሰፊው በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ። በገንዘብ ዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ መብቶች በተለያዩ የሰብአዊ መብቶችን በሚመለከት በሚወጡ ድንጋጌዎች ውስጥ የተካተቱትን የሲቪልና የፓለቲካ መብቶች የመሳሰሉትን ሊያጠቃልሉ የሚችሉ ሲሆን ፤ የገንዘብ ዋጋ ያላቸው…
እንደሌሎች መሰረታዊ መብቶች ሁሉ ለንብረት መብት ከፍተኛ ግምት የሰጠው የኢፊዴሪ ሕገ መንግስት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ እንደሚከበርለት፣ በሕግ መሰረት ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም፣ የሌሎች መብት ሳይቃረን ንብረቱ የማስተላለፍ መብቶችን ያጐናፀፈው ሲሆን የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብቻ ለንብረቱ ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ…
የሥራ ውል ተዋዋይ ወገኖች አቅዋም ሲመዘን አንድ ዓይነት የድርድር አቅም ሊኖራቸው እንደማይችል ይገመታል፡፡ አሠሪው ከሠራተኛው የኢኮኖሚ አቅም ይልቅ በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ይኸው ጥንካሬም በውሉ ስምምነት ጊዜ ሊያንፀባርቅ ይችላል፡፡ አሠሪው ሠራተኛውን ከሚፈልገው በላይ ሠራተኛው ሥራውን ይፈልጋል፡፡ በዚህ የተነሣም ተቀጣሪው ሠራተኛ በአሠሪው ፈቃድ ስር እንዲሆን ሁኔታዎች ያስገድዱታል፡፡ አሠሪው ቢኢኮኖሚው ጥንካሬ ምክንያት…
መግቢያ አንድ አሠሪ በየትኛውም ሁኔታና ዋጋ ቢሆን ከፍ ያለ ትርፍ የማግኘት ፍላጐት አለው፡፡ ሠራተኛው በሌላ በኩል ሰብዓዊ ክብሩና የሥራ ደህንነቱ ተጠብቆ የሚሠራበት ጊዜና ሁኔታ ተመቻችቶለት ለጉልበቱ ተገቢ የሆነ ክፍያ እንዲያገኝ ይፈልጋል፡፡ እኒህ ተቃራኒ የሆኑ ፍላጐቶች በአሠሪውና በሠራተኛው መካከል አለመግባባትን የመፍጠር ኃይል ያላቸው ሲሆን ችግሩን በመፍታት ረገድ ሁሉም ወገን ያሻውን እንዲያደርግ…
በልዩ ግዴታ ምክንያት የሚሰጡ አገልግሎቶች የስራ ጉዳት በደረሰ ጊዜ አሠሪው ልዩ ግዴታዎች አሉበት፡፡ ይኸውም በጊዜው የህክምና ዕርዳታ መሥጠት ተስማሚ በሆነ የመጓጓዣ ዘዴ በአቅራቢያው ወደሚገኘው የህክምና ጣቢያ ማድረስ እና የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሥራ ላይ ጉዳት መድረሱን ማሳወቅ እንዲሁም ጉዳቱ እንዲሁም ጉዳቱ ሞትን ባስከተለ ጊዜ የቀብር…
የአካል ጉዳት መጠን ደረጃዎች የአካል ጉዳት መጠን ደረጃዎች በአራት ይከፈላሉ፡፡ ይኸውም ጊዜያዊ የአካል ጉዳት ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት እና ሞት ናቸው፡፡ እንደየቅደም ተከተላቸው በሚከተለው ሁኔታ እናያቸዋለን፡፡ ሀ. ጊዜያዊ የአካል ጉዳት፡- የዚህ ጉዳት ሰለባ የሆነ ሠራተኛ የተመደበበትን ሥራ ለተወሰነ ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል ለማከናወን እንዳይችል ይሆናል አንቀጽ…
ትርጉም   በሥራ ምክንያት የሚመጣ በሽታን ትርጉም ማወቅ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ከበሽታዎች ውስጥ የትኛው በስራ ምክንያት እንደሚመጣ የትኞቹ ደግሞ በተለመደው ሁኔታ የሰውን ልጅ የሚያጠቁ  ከሥራ ጋር ያልተያያዙ እንደሆኑ ለመለየት ይረዳል፡፡ በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ ህግ መሠረት በሥራምክንያት የሚመጣ በሽታ ማለት   “ሠራተኛው ከሚሠራው የሥራ ዓይነት ወይም ሠራተኛው ከሚያከናውነው ሥራ አካባቢ የተነሣ…
በሥራ ሂደት ወይም ከሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በማናቸውም ጊዜ ያልታሰቡ አደጋዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በተለይም ዘመናዊው የኢንዱስትሪ አሠራር ሂደት እያደገና እየተወሳሰበ መምጣቱ ከመሥሪያዎቹ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አደጋ የመፈጠር ዕድሉን ሠፊ ያደርገዋል፡፡ ከድኅነት ጋር ተያይዞም ችግሩ ይከፋል፡፡ ጉዳቱም ከተጎጂው ዘልቆ በሥሩ የሚተዳደሩ ቤተሰቦቹን የሚነካ በመሆኑ ከፍ ያለ ቀውስን በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጥር ነው፡፡ …
በስራ ግንኙነት ውስጥ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ አስፈላጊነት ከሚገልጹ ምክንያቶች ውስጥ በአንድ በኩል ሰራተኛውን አግባብ ካልሆነ ብዝበዛ መከላከል በሌላ በኩል ደግሞ ሰራተኛው የሚፈለግበትን ግዴታዎች በአግባቡ እንዲወጣ ማደረግ የሚገኙበት መሆኑን ቀደም ብለን ያየነው ነው፡፡ ለዚህም ከሌሎች በተጨማሪ ሕጉ ዝቅተኛ የስራ ሰዓትን ፣ የዕረፍት ጊዜን እና የፈቃድ ጊዜ አሰጣጥን በመወሰን ይቆጣጠራል፡፡ በዚህ መልኩ…
የስራ ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ለተዋዋይ ወገኞች ፈቃድ ብቻ እንዳይተውና ህግ ጣልቃ እንዲገባ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ከስራ ውል መቋረጥ ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡ ሥለዚህም የስራ ውል በዘፈቀደ ሳይሆን በበቂ ምክንያቶች ላይ ተመስርቶ የተቋረጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ሕግ አስፈላጊውን ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ይህን የሕግ ጥበቃ ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ…
በስራ ውል የተፈጠረው የአሰሪና ሰራተኛ የስራ ግንኙነት በሚቀጥለው ክፍል ውስጥ እንደምንመለከተው ለዘለቄታው ሊቋረጥ እንደሚችል ሁሉ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል፡፡ የውሉ መታገድ ከስራ ውል መቋረጥ በመለስ ለጊዚያዊ አገልግሎት የሚደረግ የመብትና ግዴታዎች መታገድ ቢሆንም እገዳው እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ሰራተኛው ስራውን የመስራት ግዴታ አሰሪው ደግሞ በህብረት ስምምነት መሰረት በሌላ አካኋን ካልተወሰነ በስተቀር ደሞዝና ሌሎች…
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት የአሰሪው እና የሰራተኛው ጠቅላላ ግዴታዎች በሁለት አንቀጾች ስር ተካተው ይገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት አንቀጽ 12 የአሰሪውን አንቀጽ 13 ደግሞ የሰራተኛውን ግዴታዎች ይዘረዝራሉ፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ ከአዋጁ አንቀጽ 12/8/ እና 13/7/ መረዳት እንደሚቻለው ሰራተኛው በህግ የሚኖረውን መብት እስካላጠበቡ ድረስ የስራ ውል፣ የሕብረት ስምምነትና የስራ ደንብ እንደ ሁኔታው…
1. The Assembly of African Union The Assembly is the ‘supreme organ of the African Union’ composed of Heads of States and Governments.  It meets once in a year in ordinary session, and it can meet in extraordinary session at the request of any member state that has to be…